https://amh.sputniknews.africa/20260720/4710235.html
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Sputnik አፍሪካ
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፤ "በአፍሪካ 54... 20.07.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-07-20T19:52+0300
2026-07-20T19:52+0300
2026-07-20T19:54+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/14/4710082_2:0:1278:718_1920x0_80_0_0_27563a8e0eea244e11cfdf5df47241d0.jpg
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፤ "በአፍሪካ 54 ሀገራት መኖራቸውን ስናስብ፥ ይህ በጣም ትልቅ ስኬት ነው። አሁንም ከፊታችን ጊዜ አለን፤ ሂደቱም በቀጣይነት ላይ ነው። በየቀኑ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሀገራት በጉባኤው ላይ ለመገኘት ፍላጎታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።" እንደ ባሽኪን ገለጻ፥ ሞስኮ የቻድ ፕሬዚዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በጉባኤው ላይ እንደሚገኙ የሚገልጽ የጽሑፍ ማረጋገጫ በመጠባበቅ ላይ ነች። ሁለቱም ወገኖች ከጉባኤው ጎን ለጎን በፕሬዚዳንት ዴቢ እና በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የሁለትዮሽ ስብሰባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላቸውም አክለዋል።በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ የሰጡ ሀገራት መካከል፦ ማሊ፣ ማደጋስካር፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ግብፅ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ቡሩንዲ እና ሱዳን ይገኙበታል።ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጥቅምት 18 እና 19 በሞስኮ ይካሄዳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Sputnik አፍሪካ
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
2026-07-20T19:52+0300
true
PT1S
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/14/4710082_162:0:1119:718_1920x0_80_0_0_34e46b4d8688712dcca3f475cb404949.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
19:52 20.07.2026 (የተሻሻለ: 19:54 20.07.2026) ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት በጥቅምቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ ሰጡ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፤ "በአፍሪካ 54 ሀገራት መኖራቸውን ስናስብ፥ ይህ በጣም ትልቅ ስኬት ነው። አሁንም ከፊታችን ጊዜ አለን፤ ሂደቱም በቀጣይነት ላይ ነው። በየቀኑ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሀገራት በጉባኤው ላይ ለመገኘት ፍላጎታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።"
እንደ ባሽኪን ገለጻ፥ ሞስኮ የቻድ ፕሬዚዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በጉባኤው ላይ እንደሚገኙ የሚገልጽ የጽሑፍ ማረጋገጫ በመጠባበቅ ላይ ነች። ሁለቱም ወገኖች ከጉባኤው ጎን ለጎን በፕሬዚዳንት ዴቢ እና በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መካከል የሁለትዮሽ ስብሰባ ለማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላቸውም አክለዋል።
በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ማረጋገጫ የሰጡ ሀገራት መካከል፦ ማሊ፣ ማደጋስካር፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ግብፅ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ቡሩንዲ እና ሱዳን ይገኙበታል።
ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጥቅምት 18 እና 19 በሞስኮ ይካሄዳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X