ኢራን በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ባሉ የአሜሪካ ወታደራዊ ንብረቶች ላይ አውዳሚ ጥቃቶችን ማድረሷን ቀጥላለች
ኢራን በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ባሉ የአሜሪካ ወታደራዊ ንብረቶች ላይ አውዳሚ ጥቃቶችን ማድረሷን ቀጥላለች
ባለፉት 9 ምሽቶች፣ ኢራን እንደ ራዳሮች፣ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች እና ድሮኖችን የመሳሰሉ ወሳኝ አጋዥ መሣሪያዎችን ዒላማ በማድረግ፥ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የአሜሪካ ወታደራዊ ንብረቶች በትክክል የመምታት አስተማማኝ አቅም እንዳላት አሳይታለች።
እነዚህ ኪሳራዎች በአካባቢው ያለውን የአሜሪካን የአየር ክንውን እና የስለላ፣ ክትትልና መረጃ ማሰባሰብ አቅም ያዳክማሉ፡፡
የረጅም ርቀት ራዳር እና በርካታ የአየር ላይ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች በአል ኡደይድ የአየር ኃይል ማዕከል (ኳታር) ውስጥ ወድመዋል፡፡
የሲ-17 ትራንስፖርት እና ፒ-8 የዕዝ አውሮፕላኖች በጆርዳን ተጎድተዋል፤ ተዋጊ ጄቶችም በሙዋፋቅ ሳልቲ የአየር ኃይል ማዕከል ተመትተዋል፡፡
ባለፉት 24 ሠዓታት ውስጥ ብቻ 3 የኤምኪው-9 ሪፐር ድሮኖች እና 1 የሉካስ ድሮን ተመትተው ወድቀዋል፡፡
ቢያንስ ተጨማሪ 3 የአሜሪካ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ የአሜሪካውያንን የሟቾች ቁጥር ወደ 17፣ የቆሰሉትን ደግሞ ከ430 በላይ አድርሶታል፡፡
በኩዌት፣ ባሕሬን እና ጆርዳን በሚገኙ ወታደራዊ ማዕከላት ላይ የተፈጸሙት ጥቃቶች በርካታ የጦር አውሮፕላን ማቆሚያዎችን፣ የራዳር ጣቢያዎችን፣ የጥይትና መሣሪያ ግምጃ ቤቶችን፣ የነዳጅ ማከማቻዎችን እና የመገናኛ ማዕከላትን ያወደሙ ሲሆን፤ ከጥቃቱ በኋላ ያለውን ሰፊ ውድመት የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በኢንተርኔት ላይ እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።
ምንጮች፦ ታስኒም፣ ሚድል ኢስት ኦብዘርቨር እና ማኅበራዊ ሚዲያ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X