አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጣሪ እንጂ ተጠቃሚ ብቻ መሆን የለባትም - የዚምባብዌ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፈጣሪ እንጂ ተጠቃሚ ብቻ መሆን የለባትም - የዚምባብዌ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ

አዲስ በተቋቋመው የዓለም አቀፍ የሰው ሠርሽ አስተውሎት ትብብር ድርጅት መሥራች አባላት መካከል 10 የአፍሪካ ሀገራት እንደሚገኙበት የጠቀሱት ጀስቲስ ሙካሮ፤ አኅጉሪቱ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን በዝምታ ከመቀበል ባለፈ ዕድሉን በአግባቡ መጠቀም አለባት ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ከቃለ መጠይቁ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦

🟠ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት፦ ድርጅቱ በሰው ሠርሽ አስተውሎት አስተዳደር ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም ይህ በቴክኒክ ሙያ፣ በፖሊሲ አመራር እና በኢንቨስትመንት መደገፍ አለበት።

🟠ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ ራስን መቻል ማለት ራስን ማግለል ማለት አይደለም፤ ይልቁንም ወሳኝ በሆኑ መሠረተ ልማቶች እና መረጃዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ማለት ነው።

የጋራ ልማት ከቴክኖሎጂ ሽግግር ባለፈ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፦

የአገር ውስጥ ምርምርን፣

የክህሎት/የተሰጥኦ ልማትን፣

የእውቀት ልውውጥን እና

የጋራ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን።

🟠ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች፦ ሙካሮ ግብርና፣ ጤና ጥበቃ፣ ትምህርት፣ የአየር ንብረት መቋቋም እና የሕዝብ አስተዳደርን እንደ ቁልፍ ዘርፎች ለይተዋል፤ ከሰው ሠርሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት፣ ሳይበር ደህንነት እና የክህሎት ሽግግር ኢንቨስትመንቶች ጋር መተግበር እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

🟠ስጋቶች እና ዕድሎች፦ እኩል ያልሆነ ተሳትፎ፣ የተበታተኑ ፖሊሲዎች እና ደካማ የአገር ውስጥ አቅምን ያስጠነቀቁት ሙካሮ፤ ስኬታማ አጋርነቶች የረጅም ጊዜ አቅምን መገንባትና የአገር ውስጥ ፈጠራን መደገፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0