የአፍሪካ ልማት ባንክ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል የ13 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አጸደቀ
18:44 20.07.2026 (የተሻሻለ: 18:54 20.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል የ13 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አጸደቀ
የወረርሽኙ ማዕከል የሆነችው ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 11 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች፤ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ደግሞ እያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርሳቸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ የገንዘብ ድጋፍ የሚከተሉትን ተግባራት ያግዛል፦
▪ በሽታውን አስቀድሞ ለመለየት፣
▪ የበሽታ ሥርጭት ክትትል ለማድረግ፣
▪ የማኅበረሰብ ተሳትፎን ለማሳደግ፣
▪ የሕዝብ ግንዛቤ ለመፍጠር እና
▪ ቀጣናዊ ቅንጅትን ለማጠናከር።
ወረርሽኙ መከሰቱ በይፋ የተነገረው በግንቦት 15 በዲአር ኮንጎ ኢቱሪ ግዛት ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ ወደ ሰሜን ኪቩ እና ደቡብ ኪቩ ተስፋፍቷል። ወረርሽኙ የተከሰተው "ቡንዲቡግዮ" በተሰኘው አዲስ የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት ለዚህ ዝርያ የጸደቀ ክትባትም ሆነ ልዩ ሕክምና የለም።
ቪዲዮው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ሚኒስትር ኢቦላን ለመከላከል የተዘጋጁ የመድኃኒት ክምችቶችን ሲፈትሹ ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X