የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ሴቶች በማንዴራ ድንበር ተሻጋሪ የሰላም ውይይት አካሄዱ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ሴቶች በማንዴራ ድንበር ተሻጋሪ የሰላም ውይይት አካሄዱ
የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ሴቶች በማንዴራ ድንበር ተሻጋሪ የሰላም ውይይት አካሄዱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.07.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ሴቶች በማንዴራ ድንበር ተሻጋሪ የሰላም ውይይት አካሄዱ

ከኢትዮጵያ (ሱፍቱ)፣ ከኬንያ (ማንዴራ) እና ከሶማሊያ (ቤሌድ ሐዎ) የተወከሉ የሴት መሪዎች እና የሰላም ተሟጋቾች ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ አብሮ መኖርን ለማሳደግ እና በድንበር አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሱ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በማንዴራ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

ውይይቱ በድንበር አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግር፣ መፈናቀል እና የኢኮኖሚ ዕድሎች ዉሱንነት የመሳሰሉ የጋራ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታትና የሴቶችን የውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ ያለመ መሆኑን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በ‘ማንዴራ የሴቶች ለሰላምና ልማት’ ድርጅት አዘጋጅነት የተካሄደው መድረኩ፣ በሦስቱ ሀገራት የሚገኙ ተሳታፊ ሴቶች በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ድንበር ተሻጋሪ ትብብራቸውን ለማጠናከር እና ቀጣይነት ያለው ውይይት ለማድረግ በጋራ ቃል ገብተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0