“ላዳ ማለት የደሃ አባት ነው" – የላዳ ታክሲ አሽከርካሪዎች እና የቴክኒሻኖች ምስክርነት
14:04 20.07.2026 (የተሻሻለ: 14:14 20.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
“ላዳ ማለት የደሃ አባት ነው" – የላዳ ታክሲ አሽከርካሪዎች እና የቴክኒሻኖች ምስክርነት
የላዳ መኪና አምራቹ የሩሲያው ቮልስኪ አውቶሞቢል ፕላንት (ቫዝ ፕላንት) ኩባንያ ዛሬ 60ኛ ዓመቱን እያከበረ ባለበት ወቅት፣ ኢትዮጵያውያን የላዳ መኪና አሽከርካሪዎቸ እና ባለሙያዎች የተሽከርካሪውን ውለታ በማጉላት ዘምኖ በአዲስ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
"ላዳ ማለት የደሃ አባት በለው። ላዳን የፈጠረው በጣም የሚገርም ካምፓኒ ነው። ጥሩ መኪና ነው ያመረተው። .... እንደፈለግህ መጠቀም ትችላለህ።" ሲል የላዳ አሽከርካሪ እና ቴክኒሻን የሆነው አስቻለው አወቀ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡
ሌላኛው የላዳ አሽከርካሪ እና ቴክኒሻን ዘሪሁን ኃይሉ በበኩሉ፣ "እንደ ላዳ ደግሞ ጠንካራ መኪና የለም። ብዙ ቤተሰብ አስታዳድረንበታል። አሁንም እያስተዳደርንበት ነው። አሁንም እየሠራንበት ነው።" ብሏል፡፡
የላዳ መኪና አሽከርካሪዎች እና የቴክኒሻኖች ስለመኪናው ሥሪት፣ ገጠመኞቻቸውንና ለወደፊቱ ቢሆን ያሉትን የጠቆሙበት ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
የስፑትኒክ አፍሪካ ቤተሰቦች፣ እናንተም የላዳ ታክሲ ገጠመኞቻችሁን አጋሩን
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X