በ2026ቱ የሻንጋይ የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኮንፈረንስ ላይ ሮቦቶች ቀለም በመቀባት፣ እግር ኳስ በመጫወት የብዙዎችን ቀልብ ሳቡ
20:46 19.07.2026 (የተሻሻለ: 20:54 19.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ2026ቱ የሻንጋይ የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኮንፈረንስ ላይ ሮቦቶች ቀለም በመቀባት፣ እግር ኳስ በመጫወት የብዙዎችን ቀልብ ሳቡ
ቅዳሜ ዕለት መግቢያ ትኬቱ ሙሉ በሙሉ የተሸጠለትና 80,000 የሚጠጋ ሕዝብ የታደመበት ይህ ኮንፈረንስ የተካሄደ ሲሆን፤ በዕለቱም አምሳለ-ሰው ሮቦቶች ከመደነስ እና እግር ኳስ ከመጫወት ጀምሮ ቀለም የመቀባት፣ ማሳጅ የመስጠት እና ፎቶ የማንሳት ክንውንን በተግባር አሳይተዋል።
ከዓርብ እስከ ሰኞ የሚቆየው ይህ ባለ አራት ቀን መርሃ ግብር፥ ለዘመናዊ የሮቦቲክስ እና የጄኔሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ትልቅ ዓለም አቀፍ ማሳያ ሆኗል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
አንድ ሠዓሊ ሮቦት በቀጥታ ሥዕል በመሳል የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሲሆን፤ ባለ አራት እግር ሮቦት ከማንቀሳቀሻ እጅ ጋር በመሆን የፍተሻ እና የደህንነት ሥራዎችን በተግባር አሳይቷል።
እጅ የተገጠመለት የሮቦት ውሻ ደሞ በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ መስመር ፍተሻዎችን እና የደህንነት ጥበቃዎችን ማከናወን የሚችል ሲሆን፣ "ከፍተኛ ትኩረት" መሳብ ችሏል።
"የዚህን ዘመን የቴክኖሎጂ ማዕበል ተከትለናል። በዘርፉ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ተስፋ አለን" ሲሉ አንድ የዝግጅቱ ተካፋይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ሮቦቶቹ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመመልከት ቪዲዮውን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X