https://amh.sputniknews.africa/20260719/4700169.html
በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
Sputnik አፍሪካ
በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብእሁድ ዕለት አራት በአሜሪካ የሚደገፉ መርከቦች የጉዞ መፈለጊያ ሥርዓቶቻቸውን ካጠፉ በኋላ በ"አደገኛ... 19.07.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-07-19T16:43+0300
2026-07-19T16:43+0300
2026-07-19T16:44+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/13/4700016_0:0:1280:720_1920x0_80_0_0_bd8df3801bcb9c71061d3db7230d069e.jpg
በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብእሁድ ዕለት አራት በአሜሪካ የሚደገፉ መርከቦች የጉዞ መፈለጊያ ሥርዓቶቻቸውን ካጠፉ በኋላ በ"አደገኛ መስመር" ለማለፍ ሲሞክሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ ከሚገኘው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባሕር ኃይል የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለታቸውን የኢራን ወታደራዊ ኃይል አስታውቋል። "በዚህም ምክንያት ሁለቱ መርከቦች በደረሰባቸው ክስተት ሳቢያ የቆሙ ሲሆን፣ የቀሩት ሁለቱ ደግሞ ወደኋላ ተመልሰዋል" ሲል የኢራን አብዮታዊ ዘብ መናገሩን ጠቅሶ ኢቲማድ ኦንላይን የተባለው ጋዜጣ አስነብቧል።ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትቆጣጠር እና ለትራንስፖርት መርከቦች ብቸኛው አስተማማኝ መስመር በኢራን የተወሰነው ብቻ እንደሆነ አብዮታዊ ዘቡ አጽንኦት ሰጥቷል። "ቀደም ሲል እንደተገለጸው፥ ከኢራን ጋር ቅንጅት ሳይደረግ እና ፈቃድ ሳይገኝ አንዲት ጠብታ ነዳጅ፣ ጋዝ ወይም ማዳበሪያ እንኳ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፍ አይችልም" ሲል ወታደራዊ ኃይሉ አክሎ ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/07/13/4700016_160:0:1120:720_1920x0_80_0_0_58fdf5e001c659347e6f4648a7688957.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
16:43 19.07.2026 (የተሻሻለ: 16:44 19.07.2026) በሕግ ተላላፊ መርከቦች ላይ ከደረሱ ክስተቶች በኋላ ምንም ዓይነት የነዳጅ ጫኝ መርከብ ያለ ፈቃድ በሆርሙዝ ማለፍ አይችልም - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
እሁድ ዕለት አራት በአሜሪካ የሚደገፉ መርከቦች የጉዞ መፈለጊያ ሥርዓቶቻቸውን ካጠፉ በኋላ በ"አደገኛ መስመር" ለማለፍ ሲሞክሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ ከሚገኘው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባሕር ኃይል የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለታቸውን የኢራን ወታደራዊ ኃይል አስታውቋል።
"በዚህም ምክንያት ሁለቱ መርከቦች በደረሰባቸው ክስተት ሳቢያ የቆሙ ሲሆን፣ የቀሩት ሁለቱ ደግሞ ወደኋላ ተመልሰዋል" ሲል የኢራን አብዮታዊ ዘብ መናገሩን ጠቅሶ ኢቲማድ ኦንላይን የተባለው ጋዜጣ አስነብቧል።
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ እንደምትቆጣጠር እና ለትራንስፖርት መርከቦች ብቸኛው አስተማማኝ መስመር በኢራን የተወሰነው ብቻ እንደሆነ አብዮታዊ ዘቡ አጽንኦት ሰጥቷል።
"ቀደም ሲል እንደተገለጸው፥ ከኢራን ጋር ቅንጅት ሳይደረግ እና ፈቃድ ሳይገኝ አንዲት ጠብታ ነዳጅ፣ ጋዝ ወይም ማዳበሪያ እንኳ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፍ አይችልም" ሲል ወታደራዊ ኃይሉ አክሎ ገልጿል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X