በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ የአዲስ አበባ ከተማ ተቋማት ዘመናዊ መኪኖችን ተሸለሙ
16:10 19.07.2026 (የተሻሻለ: 16:24 19.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ የአዲስ አበባ ከተማ ተቋማት ዘመናዊ መኪኖችን ተሸለሙ
በበጀት ዓመቱ የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በመሥራት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የዕውቅናና የመኪና ሽልማት ተበርክቷል።
ከአምስት የካቢኔ አባል ቢሮዎች፣ ከሦስት ክፍለ ከተሞች እና ከአምስት የካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ በድምሩ ለ14 ተቋማት የመኪና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም በየደረጃው ላቅ ያለ አፈጻጸም ላሳዩ 33 ወረዳዎች እና ለተለያዩ ተቋማት (ፋይናንስ፣ ኮሙኒኬሽን፣ ሲቪል ምዝገባ፣ ኮልፌና ልደታ ክፍለ ከተማ...) የሰርተፍኬት ዕውቅና ተሰጥቷል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ "ይህ ሽልማት በየደረጃው ባሉ አመራሮችና ባለሙያዎች መካከል የውድድር መንፈስን በመፍጠር፣ በቀጣዩ በጀት ዓመት ይበልጥ ለአገልግሎት ተደራሽነትና ለሕዝብ ተጠቃሚነት በትጋት ለመሥራት የተሰጠ ትልቅ አደራ ነው" ሲሉ ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/4
© telegram sputnik_ethiopia

2/4
© telegram sputnik_ethiopia

3/4
© telegram sputnik_ethiopia

4/4
© telegram sputnik_ethiopia
1/4
© telegram sputnik_ethiopia
2/4
© telegram sputnik_ethiopia
3/4
© telegram sputnik_ethiopia
4/4
© telegram sputnik_ethiopia