በ6 ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ" የሩጫ ውድድር ዛሬ በሐረር ከተማ ፍጻሜውን አገኘ
12:25 19.07.2026 (የተሻሻለ: 12:34 19.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ6 ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ" የሩጫ ውድድር ዛሬ በሐረር ከተማ ፍጻሜውን አገኘ
መነሻና መድረሻውን ሐረር በር ላይ ባደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ማጠቃለያ ውድድር ላይ ፕሮፌሽናል አትሌቶችና ከአዲስ አበባ የተጓዙ ተሳታፊዎች መሳተፋቸውን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውድድሩ ውጤቶች፦
በወንዶች፦
ሴና ገመቹ ( 32:04:77 )
ምህረት አወቀ
ኢብራሒም መሐመድ
በሴቶች፦
ራሔል እምቢበል ( 41:43:23 )
አምራን ሽሙዝ
አዚዛ ሙክታር
በውድድሩ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ መሐመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
የ2018 የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ በደብረ ብርሃን፣ ሐዋሳ፣ ጅማ፣ በቆጂ፣ አርባምንጭ እና ሐረር ከተሞች የተካሄደ ሲሆን፣ በስድስቱም ከተሞች ለተሳተፉ 43 ተወዳዳሪዎች ሲገጣጠም የኢትዮጵያ ካርታ ቅርፅ የሚሰራ ልዩ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/6
© telegram sputnik_ethiopia

2/6
© telegram sputnik_ethiopia

3/6
© telegram sputnik_ethiopia

4/6
© telegram sputnik_ethiopia

5/6
© telegram sputnik_ethiopia

6/6
© telegram sputnik_ethiopia
1/6
© telegram sputnik_ethiopia
2/6
© telegram sputnik_ethiopia
3/6
© telegram sputnik_ethiopia
4/6
© telegram sputnik_ethiopia
5/6
© telegram sputnik_ethiopia
6/6
© telegram sputnik_ethiopia