ታንዛኒያ ከሩሲያ የወጣቶች አቅም ግንባታ ተሞክሮ መማር አለባት - ሚኒስትር ዴኤታ

ሰብስክራይብ

ታንዛኒያ ከሩሲያ የወጣቶች አቅም ግንባታ ተሞክሮ መማር አለባት -  ሚኒስትር ዴኤታ

​ሩሲያ በወጣቶች ልማት ፕሮግራሞች ላይ ሰፊና ወሳኝ ተሞክሮ ያላት ሲሆን ታንዛኒያ ደግሞ መሰል ተግባራትን ገና በመተግበር ላይ ነው ያለችው ሲሉ በፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የወጣት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ጆኤል አርተር ናናውካ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

​እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ታንዛኒያ ከሩሲያ በሚከተሉት ዘርፎች ጠቃሚ ትምህርቶችን መቅሰም ትችላለች፦

​ የወጣቶች የኢኮኖሚ አቅም ማሳደጊያ ፕሮግራሞች፣

የክህሎት ማበልጸጊያ ሥልጠና ማዕከላትን ማቋቋም፣

ለወጣቶች የፈጠራ ሥራዎች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስልቶች፣

የሥራ ላይ ልምምድ ዕድሎችን መፍጠር።

​በተጨማሪም ታንዛኒያ ወጣቶቿ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮ እንዲቀስሙና ተሰጧቸውን የሚያሳዩበት የተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ለማመቻቸት በትኩረት እንደምትሠራ ናናውካ ጠቁመዋል።

​ የናናውካ አስተያየት በቅርቡ በዳሬሰላም ወጣቶችን በማብቃት ዙሪያ ከተካሄዱት ውይይቶች በኋላ የመጣ ነው። የታንዛኒያ ባለሥልጣናት ከዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ዳይሬክቶሬት እና ከፌዴራል የወጣቶች ጉዳይ ኤጀንሲ ከተውጣጡ የሩሲያ ልዑካን ቡድን የተወያዩ ሲሆን በሩሲያ የሳይንስና ባሕል ማዕከል የጋራ ኮንፈረንስ ተካሂዶም ነበር።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0