ኡጋንዳ ከአሰቃቂው የተማሪዎች አውቶቡስ አደጋ በኋላ በመላ ሀገሪቱ የትምህርት ቤት ጉዞዎችን ማገዷን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ኡጋንዳ ከአሰቃቂው የተማሪዎች አውቶቡስ አደጋ በኋላ በመላ ሀገሪቱ የትምህርት ቤት ጉዞዎችን ማገዷን አስታወቀች

የእገዳው ውሳኔ በፍጥነት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን ተጨማሪ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ጸንቶ እንደሚቆይ የትምህርት እና ስፖርት ሚኒስትሩ ጆን ክሪሶስቶም ሙዪንጎ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አጠቃላይ የፖሊሲ ክለሳ የሚያደርግ ሲሆን የሚከተሉትን መመሪያዎች ተግባራዊ በማድረግ በትምህርት ቤት ጉዞዎች ወቅት የተማሪዎችን ደህንነት ያጠናክራል፦

▪ አስገዳጅ የአደጋ ስጋት ምዘናዎችን ማድረግ፣

▪ ግልጽ የሆኑ የወላጆች ፈቃድ ማግኘት፣

▪ በቂ የመምህራን እና የተማሪዎች የክትትል ጥምርታ፣

▪ የምሽት ጉዞዎች ጥብቅ ክልከላ።

የትምህርት ሚኒስቴሩ የአደጋውን መንስኤ ለመመርመር ከኡጋንዳ ፖሊስ ኃይል እና ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን ሙዪንጎ ጠቁመዋል።

በኡጋንዳዋ ካፕቾርዋ ከተማ በደረሰው የተማሪዎች አውቶቡስ አደጋ ሕፃናትን ጨምሮ የ21 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0