ኢትዮጵያ በጠንካራ የቁጥጥር ሕግ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎችን ጫና መቋቋም እንደቻለች ተገለጸ
18:05 18.07.2026 (የተሻሻለ: 18:14 18.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በጠንካራ የቁጥጥር ሕግ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎችን ጫና መቋቋም እንደቻለች ተገለጸ
ጂ.ጂ.ቲ.ሲ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ያጠናው ጥናት፤ በኢትዮጵያ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎች ጣልቃ ገብነት መጠን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሆነ አሳይቷል፡፡
በዚህም ሀገሪቱ ከአፍሪካ 2ኛ ከዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ጥናቱን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ለዚህ ደረጃ ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም ያወጣችው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ የቁጥጥር ድንጋጌዎች በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡
የአዋጁ ቁልፍ የቁጥጥር ድንጋጌዎች፦
▪ የትንባሆ ኢንዱስትሪዎች ከመንግሥት አካላት ጋር ምንም አይነት የጥቅም ትስስር እንዳይኖራቸው፣
▪ ኢንዱስትሪዎቹ ለመንግሥት አካላት በስጦታ ገንዘብ እንዳይሰጡ፣
▪ የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ እንዳሰማሩ ይከለክላሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X