ምዕራባውያን ‘በፖለቲካ፣ በሥነ-ሕዝብ እና በኢኮኖሚ እየሞቱ ነው’- ቡርኪና ፋሷዊ አክቲቪስት
16:57 18.07.2026 (የተሻሻለ: 17:04 18.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ‘በፖለቲካ፣ በሥነ-ሕዝብ እና በኢኮኖሚ እየሞቱ ነው’- ቡርኪና ፋሷዊ አክቲቪስት
የ 'ሲቪክ ዩዝ ፎር ሶቨርኒቲ' ማኅበር ቃል አቀባይ ጁልስ ሴዛር ዋንግሬ፤ ሁለት የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮች ከቡርኪና ፋሶ መባረራቸውን አስመልክተው ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን ሲሰጡ፤ የሽግግሩን ዋና ግቦች የሚቃወም ማንኛውም ሰው በሀገሪቱ ውስጥ እንዲቆይ ቡርኪና ፋሶ መፍቀድ የለባትም ብለዋል።
ቡርኪና ፋሶ ቀደም ሲል በ2022 እና በ2025 ሁለት የአውሮፓ ኅብረት ተወካዮችን እንዲሁም በሚያዝያ 2026 ሦስት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶችን አባርራለች።
በተጨማሪም የአውሮፓ ኅብረት “በነጻነት ምህዳራችን እና ከሩሲያ ጋር ባለን አጋርነት ላይ ጣልቃ እየገባ ነው” ብለዋል።
የዋጋዱጉ የቅርብ ጊዜ ውሳኔ ሰፋ ያለ ዓለም አቀፋዊ ለውጥን የሚያንፀባርቅ ነው ያሉት ዋንግሬ፤ በግሎባላይዜሽን የተዳከመውና “የምዕራባውያን በመባል የሚታወቀው አንዱ ዓለም ሲሞት ሌላ አዲስ ዓለም እየተወለደ መሆኑን” የሚያሳይ ነው ሲሉ አስረግጠዋል።
አዲሱ ዓለም እንደ ሩሲያ፣ ኢራን እና ህንድ ያሉትን ሀገራት እንደሚያካትትም ምልከታቸውን አጋርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X