በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ እየተባባሰ እንደመጣ እና ሁከትና ብጥብጥ የሰብዓዊ ምላሽኑ እያደናቀፈ እንደሚገኝ ኦቻ ገለጸ
15:28 18.07.2026 (የተሻሻለ: 15:34 18.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ እየተባባሰ እንደመጣ እና ሁከትና ብጥብጥ የሰብዓዊ ምላሽኑ እያደናቀፈ እንደሚገኝ ኦቻ ገለጸ
በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ መረጃ መሠረት፤ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ 2,124 ሰዎችን አጥቅቶ በታሪክ ሦስተኛው ከባድ ወረርሽኝ ሆኗል።
የታካሚዎችን ትራንስፖርት እና የሕክምና ክትትል ለማጠናከር አሥር አዳዲስ አምቡላንሶች ኢቱሪ ክልል መድረሳቸውን ኦቻ አስታውቋል።
የወረርሽኙን የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ሥራ እያወሳሰቡ ነው የተባሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች፦
▪ በሰሜን ኪቩ በተከሰተ ግጭት በአንድ ጥቃት ብቻ ቢያንስ 10 ሰዎች ሲገደሉ ሰባቱ ቆስለዋል። ጥቃቱ ከእሁድ ጀምሮ የ22 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፉ ተከታታይ ክስተቶችን ተከትሎ የመጣ ነው።
▪ የሁከቱ መባባስ ሲቪሎችን በማፈናቀል ቀድሞውኑ ወረርሽኙን እየተዋጋ ባለው አካባቢ የሰብዓዊ ረድኤት ተደራሽነትን ጭራሽኑ ገድቧል።
ኦቻ ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ፣ አስተማማኝ የሰብዓዊ ረድኤት ተደራሽነትን እንዲያረጋግጡ እና የጤና ባለሙያዎችን ደህንነት እንዲያስጠብቁ ጥሪ አቅርቧል። ቢሮው አክሎም፤ "እነዚህ ሁኔታዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር መሠረታዊ ናቸው" ብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X