ንጋት ሐይቅ ከግምታዊ ዓመታዊ የዓሣ ማጥመድ አቅሙ ከ60 በመቶ በላይ ማምረቱ ተገለፀ
14:31 18.07.2026 (የተሻሻለ: 14:34 18.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ንጋት ሐይቅ ከግምታዊ ዓመታዊ የዓሣ ማጥመድ አቅሙ ከ60 በመቶ በላይ ማምረቱ ተገለፀ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ማጠራቀሚያ ገንዳ የሆነው ንጋት ሐይቅ፤ በዓመት እስከ 15 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዓሣ የማስገኘት አቅም እንዳለው ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ10 ሺህ 595 ቶን በላይ ምርት በመሰብሰብ ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገቡን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህ ስኬት በሐይቁ ዙሪያ ከ23 እስከ 25 በሚሆኑ ማህበራት ለተደራጁ ከ1 ሺህ 600 በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
የዓሣ ምርቱም አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ለሚታየው የዓሣ ፍጆታ ፍላጎት ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል ሲል የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X