ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ አንድ የጋራ ቀጣናዊ ቪዛ ለመጀመር እያጤኑ እንደሆነ ተሠማ

© telegram sputnik_ethiopiaኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ አንድ የጋራ ቀጣናዊ ቪዛ ለመጀመር እያጤኑ እንደሆነ ተሠማ
ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ አንድ የጋራ ቀጣናዊ ቪዛ ለመጀመር እያጤኑ እንደሆነ ተሠማ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.07.2026
ሰብስክራይብ

ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ አንድ የጋራ ቀጣናዊ ቪዛ ለመጀመር እያጤኑ እንደሆነ ተሠማ

የ2027ቱን የአፍሪካ ዋንጫ በጋራ የሚያዘጋጁት ሦስቱ ሀገራት የውድድሩ ተጓዦችን ሂደት ለማቅለል የሰነቁት ውጥን እንደሆነ ታውቋል።

እንደ ባለሥልጣናት ገለጻ ዕቅዱ የሚከተሉት ዓላማዎች አሉት፦

የድንበር ማቋረጫ ሂደቶችን ማቅለል፣

ለደጋፊዎች እና ጎብኝዎች እንከን የለሽ የድንበር ዘለል ጉዞን ማስቻል፣

በውድድሩ ወቅት ቀጣናዊ ቱሪዝምን ማሳደግ።

የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ በዚህ የምስራቅ አፍሪካ ክፍል ሲካሄድ የመጀመሪያው ይሆናል። ውድድሩ የቀጣናዊ ትብብር መንፈስን በሚያንጸባርቀው የስዋሂሊ "ፓሞጃ" (አንድነት) መፈክር ስር ይካሄዳል።

የቀረበው የቪዛ ሃሳብ እ.ኤ.አ በ2014 በኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ የተጀመረውን የምስራቅ አፍሪካ የቱሪስት ቪዛ መሠረት ያደረገ ነው። ይህ ቪዛ በአሁኑ ጊዜ ተጓዦች በ100 ዶላር ፈቃድ ሦስቱንም ሀገራት እስከ 90 ቀናት እንዲጎበኙ ያስችላቸዋል።

አሠራሩ በሦስቱ የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅ ሀገራት ሥራ ላይ መዋሉ እንደ የተግባር ሙከራ እንደሚያገለግል ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ስኬቱ በምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ውስጥ ለሰፊ የነፃ እንቅስቃሴ መንገድ ሊከፍት ይችላል ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0