"አንድ ጀልባ በሁለት ካፒቴኖች አይመራም" - ኢብራሂም ትራኦሬ በሥልጣን ሽግግር ዙሪያ

ሰብስክራይብ

"አንድ ጀልባ በሁለት ካፒቴኖች አይመራም" - ኢብራሂም ትራኦሬ በሥልጣን ሽግግር ዙሪያ

​የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ በያድጋ ክልል ከብሔራዊ ኃይሎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፤ አሁን ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ቶማስ ሳንካራ ከተገደሉበት እና ብሌዝ ኮምፓኦሬ ሥልጣን ከያዙበት እ.ኤ.አ ከ1987ቱ ክስተት ጋር በማነጻጸር ግምታዊ ወሬዎችን ለማስተባበል ሞክረዋል።

ትራኦሬ እ.ኤ.አ 2022 ጥቅምት ወር ስለመሩት መፈንቅለ መንግሥት ሲናገሩ፤ "ከወታደሮቼ ጋር ስንቀሳቀስ ግንባር ቀደም ሆኜ ነው፤ ከእኔ ፊት የነበረ አንድም ወታደር አልነበረም" ብለዋል።

ሁለቱ ሁኔታዎች በፍጹም ሊነጻጸሩ እንደማይችሉ የሞገቱት ፕሬዚዳንቱ፤ ቪላ ውስጥ ተሸሽገው ትዕዛዝ እንዳልሰጡ እና በዕለቱ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ለመታየት ብቻ እንዳልመጡ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ የተሳሳቱ ንጽጽሮች እንዳይደረጉ ያሳሰቡ ሲሆን “ቁጥር አንድ፣ ቁጥር ሁለት ወይም ምንም ዓይነት ቁጥር የለም” ብለዋል።

ትራኦሬ “ተልዕኮ” እንዳላቸው በመግለጽ፤ ቡድናቸውም ይህንኑ ተልዕኮ “እየተከተለ” መሆኑን አስገንዝበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0