የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ300 ሜጋ ዋት የግል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ110 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ300 ሜጋ ዋት የግል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ110 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ300 ሜጋ ዋት የግል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ110 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.07.2026
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ለመጀመሪያው የኢትዮጵያ የ300 ሜጋ ዋት የግል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የ110 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ

ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮጀክት አጠቃላይ ግምታዊ ወጪው 508 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ባንኩ በራሱ ከሚሸፍነው ውጭ 381.1 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር ገንዘብ ከልማት ፋይናንስ ተቋማት በማሰባሰብ ያግዛል።

በ "አሜአ ፓወር" ኩባንያ የሚለማውና የሚተዳደረው ይህ ፕሮጀክት፤ በሶማሌ ክልል ዓይሻ አቅራቢያ የሚገነባውን የ300 ሜጋ ዋት አዲስ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ ሥራ ማስጀመር እና ጥገና ሥራዎችን ያጠቃልላል።

ፕሮጀክቱ የ5 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እና አሁን ያለውን የዓይሻ 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማሻሻል ሥራዎችንም ይደግፋል ሲል ባንኩ ባሠራጨው መግለጫ አስታውቋል።

ለ25 ዓመታት በሚቆየው የኃይል ግዥ ስምምነት፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብቸኛው የኃይል ገዥ የሚሆን ሲሆን ግንባታቸው የተጠናቀቁትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ባለቤትነትም ይረከባል።

የባንኩ የኢነርጂ ፋይናንስ ሶሉሽንስ፣ ፖሊሲ እና ሬጉሌሽንስ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ዋሌ ሾኒባሬ፤ "ዓይሻ ፕሮጀክት መንግሥታት፣ የልማት አጋሮችና የግል ባለሀብቶች የፋይናንስ ተደራሽነት ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ቆርጠው ሲነሱ ምን ሊሳካ እንደሚችል ያሳየ ነው" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0