ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የአሜሪካን የምርጫ ጣልቃ ገብነት ክስ ውድቅ አደረጉ
18:00 17.07.2026 (የተሻሻለ: 18:04 17.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የአሜሪካን የምርጫ ጣልቃ ገብነት ክስ ውድቅ አደረጉ
ሩሲያ በምንም መልኩ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ያሳደረችው ተጽዕኖ የለም ያሉት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፤ ሞስኮ በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ውስጥ መቼም ቢሆን ጣልቃ ገብታ እንደማታውቅ አጽንኦት ሰጥተዋል።
አሜሪካ ቻይና "በምርጫ ጣልቃ ገብታለች" በማለት ያቀረበችው ክስ ሙሉ በሙሉ መሠረተ ቢስ እና ተንኮል አዘል መሆኑን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን በዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ አመልክተዋል።
እስራኤል አሜሪካን አታላ "ልታሸንፈው የማትችለውና መርጣ በገባችበት ጦርነት" ውስጥ ከታታለች ሲሉ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሐሙስ ለአሜሪካ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር፤ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ለአሜሪካ የምርጫ ሥርዓት "ስጋት ናቸው" ሲሉ ከሰው ነበር። ፕሬዚዳንቱ በተለይ ቻይና የ220 ሚሊዮን አሜሪካውያን መራጮችን መረጃ ማግኘቷን እና እ.ኤ.አ በ2020 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ለጆ ባይደን የሚጠቅሙ የሐሰት የምርጫ ካርዶችን ለማዘጋጀት መሞከሯን በክሳቸው ጠቅሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X