የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ለሊቢያ ግጭት መራዘም አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ ሚኒስትሩ ገለጹ
14:33 17.07.2026 (የተሻሻለ: 14:34 17.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ለሊቢያ ግጭት መራዘም አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ ሚኒስትሩ ገለጹ
በሊቢያ የተመድ ድጋፍ ልዑክ የሊቢያን ችግሮች መፍታት እንዳልቻለና "ከመፍትሔነት ይልቅ እራሱ የችግሩ አካል ሆኗል" ሲሉ በሊቢያ ፓርላማ ለተሰየመው መንግሥት የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ኢሳ አብደልመጂድ መንሱር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
ልዑኩ የምሥራቁን መንግሥት ሕጋዊነትም ሆነ ፓርላማው በምዕራቡ መንግሥት ላይ ላሳለፈው የመተማመኛ እጦት ውሳኔ እውቅና ባለመስጠት ለቀጠለው የሊቢያ የፖለቲካ ክፍፍል አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ አክለዋል።
ሚኒስትሩ የተመድ ልዑክ የሀገሪቱን የአስተዳደር ተቋማት አንድ ለማድረግ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይችላል በሚለው ሃሳብ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ℹ ሊቢያ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ እ.ኤ.አ በ2011 ባደረገው ጣልቃ ገብነት በተፈጠረው ልዩነት፤ ትሪፖሊ መቀመጫውን ባደረገውና በተመድ በሚደገፈው የምስራቁ መንግሥት የተከፈለች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ወገኖች ጦሩን እና ሀገራዊ ተቋማትን ለማዋሃድ እየተደራደሩ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X