የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የዕዳ ጫና እና የዓለም አቀፍ ገበያ የዋጋ መዋዠቅ አሁንም ኢኮኖሚውን እየፈተነ እንደሚገኝ ገለጸ
14:16 17.07.2026 (የተሻሻለ: 14:24 17.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የዕዳ ጫና እና የዓለም አቀፍ ገበያ የዋጋ መዋዠቅ አሁንም ኢኮኖሚውን እየፈተነ እንደሚገኝ ገለጸ
ማኅበሩ 23ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን "አዲሱ ዓለም አቀፋዊ እውነታ፦ ልማት፣ የመቋቋም አቅም እና የኢኮኖሚ ሽግግርን በድጋሚ ማጤን" በሚል መሪ ቃል እንዳካሄደ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሀና ምጣኔ ሀብታዊ ማሻሻያዎቹ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን ገልጸው፤ ሆኖም ኢኮኖሚው አሁንም ለከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ ለሀገር ውስጥ ግጭቶችና ለውጫዊ ጫናዎች ተጋላጭ ሆኖ መቀጠሉን አስገንዝበዋል።
“ቀደም ሲል ወደ 9% ዝቅ ብሎ የነበረው የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት በፈረንጆቹ ግንቦት 2026 መልሶ ወደ 13.4% ከፍ ማለቱ የችግሩን አሳሳቢነት ያሳያል” ብለዋል።
የተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ትርጉም ያለው የሚሆነው ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የዜጎችን ገቢ በማሳደግና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማሻሻል ወደ ተጨባጭ የሕዝብ የኑሮ ለውጥ ሲተረጎም ብቻ መሆኑን ፕሮፌሰር ታሰው አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X