የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የኤአይ ቴክኖሎጂዎችን ለጠላታዊ ዓላማዎች እየተጠቀሙባቸው ነው - የሩሲያ ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የኤአይ ቴክኖሎጂዎችን ለጠላታዊ ዓላማዎች እየተጠቀሙባቸው ነው - የሩሲያ ባለሥልጣን

​በሻንጋይ ከተከፈተው የዓለም የሰው ሠራሽ  ኮንፈረንስ ጎን ለጎን የፕሬዚዳንት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክስም ኦሬሽኪን የሰጧቸው ሌሎች መግለጫዎች፦

​▪ አዲስ የተቋቋመው የዓለም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ትብብር ድርጅት (ዊኮ) የሰው ሠራሽ አስተውህሎትን (ኤአይ) በመቆጣጠር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፣

​▪ ከሁሉም የዊኮ መስራች ሀገራት ቻይና እና ሩሲያ በኤአይ ልማት ረገድ የላቀ ስኬት አስመዝግበዋል፣

​▪ ሩሲያ እና ቻይና በሻንጋይ በነበራቸው ቆይታ በኤአይ ትብብር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን በኩባንያዎቻቸው መካከል ያለው አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ይሸጋገራል፣

​▪ ሩሲያ የራሷን የኤአይ መፍትሄዎች ለአጋር ሀገራት የምታቀርብ ሲሆን እነዚህም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ውስጥ ተግባር ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፣

​▪ ሩሲያ በኤአይ ሳቢያ የሚደቀኑ ስጋቶችን በመከላከል ረገድ ሰፊ ልምድ አላት፣

​▪ ሩሲያ የኤአይ ቴክኖሎጂዎችን በኢኮኖሚው ውስጥ በመተግበር ረገድ ከዓለም መሪ ሀገራት አንዷ ነች፣

​▪ አሜሪካ የኤአይ ቴክኖሎጂዎችን ለሌሎች የማታጋራው በቴክኖሎጂው ሌሎችን ለመበዝበዝ በማሰብ ነው። በአንጻሩ የሩሲያ እና የቻይና ኤአይ ሞዴሎች ለሁሉም ተደራሽ ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0