የሩሲያ ቋንቋ ከተቃዋሚዎች ጥረት በተቃራኒ በውጭ ሀገራት ሕያው ሆኖ ቀጥሏል - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
21:06 16.07.2026 (የተሻሻለ: 21:14 16.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ቋንቋ ከተቃዋሚዎች ጥረት በተቃራኒ በውጭ ሀገራት ሕያው ሆኖ ቀጥሏል - የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
በዓለም ዙሪያ የሩሲያ ቋንቋ ያለውን ስፍራ ለማስጠበቅ የታለሙ ፕሮጀክቶችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በቋሚነት እንደሚደግፍ ማሪያ ዛካሮቫ "የሩሲያ ግላጎል" ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር ጎን ለጎን ገልጸዋል።
"ውድድሩ (ፈጽሞ ግልጽ ባልሆነ፣ አሳማሚ እና ጤናማ ባልሆነ ሁኔታ) ቋንቋውን ለማጥፋት ከሚፈልጉ አካላት ጥረት በተቃራኒ የሩሲያ ቋንቋ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በሰፊው በሚነገርበት ሞልዶቫ መጀመሩ ትልቅ ምሳሌያዊ ትርጉም አለው" ብለዋል።
ዛካሮቫ ለፕሮጀክቱ ረጅም ዕድሜ በመመኘት፤ መሰል ውጥኖች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያስተሳስረውን የበለጸገ የባሕል ትውፊት ለመጠበቅና ለማሳደግ እንደሚረዱ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
"የሩሲያ ግላጎል" ውድድር ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የሩሲያ ቋንቋ ተናጋሪ ጸሐፊዎችን፣ ገጣሚዎችን፣ ተውኔት አዘጋጆችን እና ተርጓሚዎችን በአንድ ላይ የሚያገናኝ ሲሆን የውድድሩ ማመልከቻ እስከ ጷግሜ 5 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X