ቻይና አሜሪካን በመብለጥ የኢትዮጵያ ቡና ሦስተኛዋ ግዙፍ ገዥ ሆነች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopiaቻይና አሜሪካን በመብለጥ የኢትዮጵያ ቡና ሦስተኛዋ ግዙፍ ገዥ ሆነች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን
ቻይና አሜሪካን በመብለጥ የኢትዮጵያ ቡና ሦስተኛዋ ግዙፍ ገዥ ሆነች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2026
ሰብስክራይብ

ቻይና አሜሪካን በመብለጥ የኢትዮጵያ ቡና ሦስተኛዋ ግዙፍ ገዥ ሆነች - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን

በተጠናቀቀው የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ኢትዮጵያ 47,836 ቶን ቡና ወደ ቻይና በመላክ፤ 347 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አግኝታለች።

⬆ ይህም በቀደመው በጀት ዓመት ወደ እስያዊቷ ሀገር ከተላከው 34,284 ቶን ቡና እና ከተገኘው 219 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

ሳዑዲ አረቢያ እና ጀርመን በ2018 ዓ.ም ቀዳሚ እና ሁለተኛ የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻዎች ናቸው።

“ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ትልቋ የኢትዮጵያ ቡና ገዥ ትሆናለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ተናግረዋል።

እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ የዕድገቱ ምክንያቶች፦

▪ ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) የቡና ኤክስፖርት፣

▪ የተሻሻሉ የመላኪያ አገልግሎቶች፣

▪ እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት የንግድ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት።

“ጠንካራ የማስተዋወቅ ሥራዎችን በመሥራት እና የቻይናውያን ተጠቃሚዎችን በተለይም እያደገ የመጣውን የወጣቶች ፍላጎት ለማሟላት ኦርጋኒክ ቡና በመላክ በቻይና ያለውን ሰፊ የገበያ ዕድል ለመጠቀም እየጣርን ነው” ሲሉም አክለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0