የአፍሪካ ኀብረት ሊቀመንበር በቡርኪና ፋሶ ጎብኝታቸው ለሀገሪቱ አንድነት፣ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ
የአፍሪካ ኀብረት ሊቀመንበር በቡርኪና ፋሶ ጎብኝታቸው ለሀገሪቱ አንድነት፣ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ
የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካራሞኮ ዣን-ማሪ ትራኦሬ፤ የማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጉብኝት የኀብረቱን አጋርነት እንዲሁም ከአባል ሀገራት ጋር አኀጉራዊ ተግዳሮቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኝነቱን የሚያሳይ መሆኑን ዛሬ በዋጋዱጉ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ኀብረት ከቡርኪና ፋሶ የሰላም፣ የጸረ-ሽብርተኝነት እና የደህንነት ጥረቶች ጎን መቆሙ የዩሱፍ ጉብኝት ዋነኛ መልዕክት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ኀብረቱ ለሰብዓዊ፣ ጤና እና ልማት ድጋፎች ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል ብለዋል።
ቡርኪና ፋሶ የአፍሪካ የዲሞክራሲ፣ ምርጫዎች እና አስተዳደር ቻርተርን ቀድመው ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የጠቀሱት ሊቀመንበሩ፤ የአፍሪካ ኀብረት የቡርኪና ፋሶን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነት እንደሚያከብር በድጋሚ አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ ኀብረት ሊቀመንበር የክልላዊ ትብብር አስፈላጊነትንም አጽንኦት ሰጥተው ያብራሩ ሲሆን በሳኀል ከፍተኛ ተወካያቸው የሆኑት ማማዱ ታንጋራ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በቅርበት እንደሚሠሩ ለሚኒስትሩ ገልጸውላቸዋል።
ትራኦሬ፤ ቡርኪና ፋሶ ለአፍሪካ ኀብረት ተቋማዊ ማሻሻያ የፀና ቁርጠኝነት እንዳላት በመግለጽ ውይይቱን በደስታ ተቀብለዋል። በተጨማሪም ከኀብረቱ ጋር የሀገር ውስጥ ሀብትን በማሰባሰብ ረገድ የፋይናንስ ነጻነት ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X