የሩሲያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች እስር ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚጻረር ነው - የሕግ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች እስር ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚጻረር ነው - የሕግ ባለሙያ
የሩሲያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች እስር ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚጻረር ነው - የሕግ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች እስር ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚጻረር ነው - የሕግ ባለሙያ

“የፈረንሳይ የፍትሕ አካላት ሊመረምሯቸው የሚገቡ በርካታ የወንጀል መዝገቦችና ከባድ ወንጀሎችን ችላ ብለው ትኩረታቸውን በሙሉ በዚህ መዝገብ ላይ አድርገዋል። በሌላ በኩል በዶንባስ ለሚገኙ ሕፃናትና ንጹሐን ዜጎች ሰብዓዊ ረድኤት የምታሰባስብን ሴት ለማሳደድ ግን ጊዜ አያጡም” ሲሉ ሊባኖሳዊው የሕግ ባለሙያ ዶክተር ዑመር ናሻቤህ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

​ ይህ ዓይነቱ እርምጃ “ምዕራባውያን በግጭት ቀጣናዎች በሚከናወኑ ሰብዓዊ ተግባራት ዙሪያ ድርብ መስፈርት እንደሚከተሉ ያሳያል” ሲሉ ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተዋል። የፈረንሳይ እርምጃ ሩሲያን እንደ ጠላት የመቁጠር አባዜ ላይ የተመሠረተ መሆኑና “በቀውስ ወቅት ለንጹሐን ዜጎች ጥበቃና ድጋፍ እንዲደረግ የሚደነግገውን” የጄኔቫ ስምምነት ችላ እንዳለም አስረድተዋል።

​ አክለውም፤ ምዕራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ እንደሚደርጉት፤ ይህ የክስ ሂደትም በከፍተኛ ደረጃ ፖለቲካዊ እንጂ እውነታ ወይም ምክንያታዊነትን መሠረቱ ያደረገ አለመሆኑን ገልጸዋል።

​ የፈረንሳይ የመረጃ ተቋም እ.ኤ.አ በጥር 2025 የቀረበን ሪፖርት ተገን አድርጎ ኖቪኮቫን ለውጭ ሀገር መንግሥት መረጃ በመሰብሰብ ከሶ ምርመራ ጀምሯል። ለዶንባስ ንጹሐን ዜጎች ምግብ፣ መድኃኒትና አልባሳትን የሚያቀርበው የ “ኤስ ኦ ኤስ ዶንባስ” በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራች የሆነችው አና ኖቪኮቫ፤ በአሁኑ ወቅት በስለላ ወንጀል ተከሳ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይጠብቃታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0