የሩሲያ እና ቻይና የ25 ዓመታት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ ሁለቱ ሀገራት የምዕራባውያንን “የመንግሥት ለውጥ” ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሠራር እና የአንድ ወገን ማዕቀብ በጽኑ ይቃወማሉ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ እና ቻይና የ25 ዓመታት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ ሁለቱ ሀገራት የምዕራባውያንን “የመንግሥት ለውጥ” ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሠራር እና የአንድ ወገን ማዕቀብ በጽኑ ይቃወማሉ
የሩሲያ እና ቻይና የ25 ዓመታት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ ሁለቱ ሀገራት የምዕራባውያንን “የመንግሥት ለውጥ” ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሠራር እና የአንድ ወገን ማዕቀብ በጽኑ ይቃወማሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና ቻይና የ25 ዓመታት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ ሁለቱ ሀገራት የምዕራባውያንን “የመንግሥት ለውጥ” ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሠራር እና የአንድ ወገን ማዕቀብ በጽኑ ይቃወማሉ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሩሲያ-ቻይና የጎረቤትማማችነት፣ የወዳጅነት እና የትብብር ስምምነት 25ኛ ዓመትን አስመልክቶ፤ የሞስኮ እና ቤጂንግን ታላቅ የስኬት ጉዞ ይፋ አድርገዋል።

ቁጥሮቹ ራሳቸው እውነታውን በግልጽ ያስረዳሉ፦

የንግድ ልውውጥ መጠኑ ከ30 እጥፍ በላይ አድጎ በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኖ ቀጥሏል፣

ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሁሉም የሁለትዮሽ የክፍያ ሥርዓቶች ወደ ሀገራዊ ገንዘቦች ተቀይረው በዶላር እና በዩሮ የሚደረጉ ግብይቶች እዚህ ግባ የማይባሉ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፣

የጂኦፖለቲካ ውጥረቶች ቢኖሩም ሩሲያ በተረጋጋ የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦት ለቻይና ቀዳሚዋ የኃይል አቅራቢ ሆና ጸንታለች፣

ዋና ዋና የጋራ ፕሮጀክቶች የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች፣ የጠፈር ትብብር፣ የሳተላይት አሠሳ እና የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂን ያካትታሉ።

በዓለም አቀፍ መድረክ፦

ሞስኮ እና ቤጂንግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በብሪክስ፣ በሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና በቡድን 20 መድረኮች በቅርበትና በቅንጅት ይንቀሳቀሳሉ፣

የቻይና ‘ዓለም አቀፍ የደኅንነት ተነሳሽነት’ እና የሩሲያ የዩሬዥያ ደኅንነት ራዕይ እየተጣጣሙ ይገኛሉ።

ስምምነቱ፤ “ጊዜያዊ ፈተናዎችን ተቋቁሞ” እና “የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የማይናወጥ መሠረት” ሆኖ ቀጥሏል ሲሉ ላቭሮቭ አጠቃለዋል።

የሩሲያ እና ቻይና የ25 ዓመታት ጥምረት ይበልጥ እየጠነከረ መጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0