ናይጄሪያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ የሠራተኛ አስተዳደሯን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማደረግ መወጠኗ ተገለጸ
16:26 16.07.2026 (የተሻሻለ: 16:34 16.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ የሠራተኛ አስተዳደሯን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማደረግ መወጠኗ ተገለጸ
የሀገሪቱ የሥራ እና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሐመዱ ዲንጊያዲ፤ የመንግሥትን የሠራተኛ ማሻሻያ ስኬት በከፍተኛ ደረጃ በጠንካራ የግል ዘርፍ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።
“ዘላቂ የሥራ ዕድል ሊገኝ የሚችለው ኢንቨስት ከሚያደርጉ፣ አዳዲስ አሠራሮችን ከሚያስተዋውቁ፣ ምርትን ከሚያስፋፉ እና ለናይጄሪያውያን ዕድሎችን ከሚፈጥሩ የንግድ ተቋማት ነው” ሲሉ መናገራቸው ተጠቅሷል።
አክለውም፤ የሠራተኛ አስተዳደሩ ለማኅበራዊ ውይይቶች እና ለቀልጣፋ የግጭት መፍቻ ሥርዓቶች ትኩረት በመስጠት፤ ለኢኮኖሚ ዕድገት ስትራቴጂካዊ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በድጋሚ እየተቀረጸ መሆኑን ገልጸዋል።
“...የፌዴራል መንግሥት የንግድ ሥራ ሁኔታን ለማሻሻል፣ የባለሀብቶችን እምነት ለማጠናከር እና የድርጅቶችን ዕድገት የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን ለማስፋፋት ቁርጠኝነቱን ይቀጥላል።”
እርምጃዎቹ የሚከተሉትን ሥርዓቶች ይበልጥ ለማሻሻል ያለሙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፦
▪ የሕዝብ የሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን፣
▪ የሠራተኛ ገበያ መረጃ ሥርዓቶችን፣
▪ የሙያ ሥልጠናና ምክር አገልግሎትን።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X