የቻይና ቡና አቀነባባሪ ኩባንያ በኢትዮጵያ የተቀናጀ የቡና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
16:14 16.07.2026 (የተሻሻለ: 16:24 16.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቻይና ቡና አቀነባባሪ ኩባንያ በኢትዮጵያ የተቀናጀ የቡና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
የሁዪቺዋን ዩንግዩ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የቡና ማቀነባበር ዘርፍ መሰማራት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ኩባንያው በቡና ዘርፍ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍላጎት ወደ ተገባር ለመቀየር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።
በቻይና ሄናን ግዛት የቡና ማቀነባበሪያ ፓርክ የሚንቀሳቀሰው ይህ ኩባንያ፤ የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X