የፈረንሳዩ የዶንባስ በጎ አድራጎት ሠራተኛ የይስሙላ የፍርድ ሂደት በሩሲያ ላይ ለሚሰነዘረው ጥላቻ የሚቀርበውን ተቃውሞ ‘ለማምከን’ ያለመ ነው - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopiaየፈረንሳዩ የዶንባስ በጎ አድራጎት ሠራተኛ የይስሙላ የፍርድ ሂደት በሩሲያ ላይ ለሚሰነዘረው ጥላቻ የሚቀርበውን ተቃውሞ ‘ለማምከን’ ያለመ ነው - ተንታኝ
የፈረንሳዩ የዶንባስ በጎ አድራጎት ሠራተኛ የይስሙላ የፍርድ ሂደት በሩሲያ ላይ ለሚሰነዘረው ጥላቻ የሚቀርበውን ተቃውሞ ‘ለማምከን’ ያለመ ነው - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.07.2026
ሰብስክራይብ
የፈረንሳዩ የዶንባስ በጎ አድራጎት ሠራተኛ የይስሙላ የፍርድ ሂደት በሩሲያ ላይ ለሚሰነዘረው ጥላቻ የሚቀርበውን ተቃውሞ ‘ለማምከን’ ያለመ ነው - ተንታኝ

​በ ‘ኤስ.ኦ.ኤስ ዶንባስ’ መሥራች አና ኖቪኮቫ ላይ የተመሠረተው የወንጀል ክስ የፈረንሳይ እና የአውሮፓ ኅብረት ሰፋ ያለ ፖሊሲ አካል እና “መንግሥት በሩሲያ ላይ ለያዘው ይፋዊ የጥላቻ አቋም በሀገር ውስጥ የሚነሳን ተቃውሞ በማፈን ተቃዋሚዎችን የማስፈራራትና የማምከን ዓላማ ያለው ነው” ሲሉ ገለልተኛ ፈረንሳዊ የጂኦፖለቲካ ተንታኝ ኮም ካርፐንቲየር ደ ጉርዶን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


​“በእርግጥ ለሩሲያ የሚደረግ ማንኛውም ድጋፍ፣ ከሩሲያ (የመንግሥት) ሚዲያዎች የሚወጡ የዜና ዘገባዎችን፣ አስተያየቶችን ወይም ትችቶችን መጥቀስ ወይም ማሠራጨት በፈረንሳይ ከጠላት ጋር እንደ መመሳጠር እና ምናልባትም እንደ ሀገር ክህደት ወንጀል ሊቆጠር ይችላል። ሩሲያ በተግባር እንደ ጠላት ሀገር ነው የምትቆጠረው።"


ነገር ግን ሕጉ ከሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ “ግልፅነት” ስለሌለው አቃቤ ሕግ ፈተናዎች ሊገጥሙት ይችላሉ። ተከሳሿ 'ዩክሬን የፈረንሳይ አጋር ወይም የኔቶ አባል አይደለችም፤ ፈረንሳይም በሩሲያ ላይ ጦርነት አላወጀችም' የሚል መከራከሪያ በማንሳት የፈረንሳይ መንግሥትን አቋም ከተቃወመች የፍርድ ሂደቱ እጅግ አወዛጋቢ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0