ኸርት አታክ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ “ኢንቲማ" የተሰኘ ግዙፍ የሕክምና ከተማ ለመገንባት ተስማሙ
19:42 15.07.2026 (የተሻሻለ: 19:44 15.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኸርት አታክ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ “ኢንቲማ" የተሰኘ ግዙፍ የሕክምና ከተማ ለመገንባት ተስማሙ
በቢሾፍቱ አዲሱ አየር ማረፊያ አጠገብ በ10 ሄክታር ላይ የሚገነባው “ኢንቲማ ሄልዝኬር ሲቲ”፤ የንግድ አገልግሎትን ከነፃ ሕክምና ጋር ያቀናጃል። ዓላማውም ከንግድ ሕክምና በሚገኝ ገቢ ለአቅመ-ደካሞች የሚሰጠውን የነፃ ልብ ሕክምና በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
የአጋርነቱ ዋነኛ አካል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጥምረት የሚተገበረው የሕክምና ቱሪዝም ፕሮግራም ነው። ውጥኑ ኢትዮጵያውያን ለከፍተኛ የሕክምና አገልግሎት ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዙበትን ልማድ ለመቀልበስ እና በተመሳሳይ ኢትዮጵያን የቀጣናው የሕክምና ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።
ግዙፍ የሕክምና ከተማው ከልብ ሕክምና ባሻገር የሚከተሉትን ዘርፎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች አካቶ ይይዛል፦
▪ የካንሰር ሕክምና፣
▪ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣
▪ የነርቭ ሕክምና፣
▪ የድንገተኛ አደጋ ሕክምና።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X