በቡርኪና ፋሶ እና አፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተሻሻለ ነው - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopiaበቡርኪና ፋሶ እና አፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተሻሻለ ነው - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በቡርኪና ፋሶ እና አፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተሻሻለ ነው - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.07.2026
ሰብስክራይብ

በቡርኪና ፋሶ እና አፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተሻሻለ ነው - የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

​የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማነቃቃት ባለመ የሦስት ቀን የቡርኪና ፋሶ ጉብኝታቸው ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል።

​"በአኀጉራችን የሚታዩ በርካታ የጋራ ችግሮች በአጋርነት እና በአብሮነት ሊፈቱ ይችላሉ" ሲሉ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል።

​ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የአኅጉራዊ ተቋም መሪ ከሆኑ በኋላ በሳኀል ሀገራት እያደረጉት ባለው ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡርኪናፋ ሶን በመጎብኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን መግለጻቸውን መግለጫው ጠቅሷል።

​"ቡርኪና ፋሶ የኅብረታችን አባል እና የአፍሪካ አንድነት መሥራች ሀገር ናት" ሲሉ ሊቀመንበሩ አክለዋል።

​ℹ ቡርኪና ፋሶ እ.ኤ.አ በ2022 ከተደረገው የሥልጣን ለውጥ በኋላ ከአፍሪካ ኅብረት ተሳትፎ መታገዷ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0