“ፖለቲካችን በኃይለ ቃል ተጀምሮ በኃይል እርምጃ የሚደመደም ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ሰብስክራይብ

“ፖለቲካችን በኃይለ ቃል ተጀምሮ በኃይል እርምጃ የሚደመደም ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የፖለቲካ ስብራቶች የሚያስቀር ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

ዛሬ የተጀመረው ምክክር በኢትዮጵያ እሴትና ባሕል እየተቃኘ ቢመራ ለመጪው ትውልድ እንደሚጠቅም በማሳሰብ ተሳታፊዎች ሀገራቸውንና ልጆቻቸውን እያሰቡ እንዲመካከሩም ጥሪ አቅርበዋል።

አራት ሺህ ዜጎች በሚሳተፉበት ሀገራዊ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ መርኃ-ግብር ላይ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደተገኙ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0