ፈረንሳይ በዶንባስ የረድኤት ድርጅት መስራች ላይ የወሰደችው እርምጃ የአውሮፓ ኅብረትን የይስሙላ የሕግ የበላይነት መመዘኛዎች እንኳ ያላሟላ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ
ፈረንሳይ በዶንባስ የረድኤት ድርጅት መስራች ላይ የወሰደችው እርምጃ የአውሮፓ ኅብረትን የይስሙላ የሕግ የበላይነት መመዘኛዎች እንኳ ያላሟላ ነው - የፖለቲካ ተንታኝ
የአና ኖቪኮቫ የፍርድ ሂደት “የአውሮፓ ኅብረት ሦስቱን የኦርዌሊያን መፈክሮች ማለትም — ዲሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት እና የሰብዓዊ መብቶች መከበርን እንኳ ያልተከተለ ነው” ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር ግሬግ ሲመንስ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
◾ በኖቪኮቫ ላይ የተወሰደው “ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ” እርምጃ “የትኛውንም አማራጭ አመለካከቶች ለማፈን እየተደረገ ያለው ሰፊ ጥረት ቀጣይ አካል” እና ከዚህ ቀደም በሩሲያ የውጭ መገናኛ ብዙኃን ላይ የተጣሉ እገዳዎች፣ ማዕቀቦች እና በተቺዎች ላይ የተከፈቱ የኢኮኖሚ ጦርነቶችን የተከተለ ነው። ይህ ሁኔታ በጊዜ ሂደት መስፋቱ እንደማይቀር ሲመንስ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
◾ የኖቪኮቫ እስራት እና የፍርድ ሂደት “በሕግ ሰበብ የሚካሄድ ጦርነት” እንዲሁም በዩክሬን ዙሪያ ያለውን ትርክት ይበልጥ አጥብቆ ለመቆጣጠር የተደረገ “የሙከራ ጉዳይ” ነው።
◾ ከፈረንሳይ መንግሥት እየጨመረ የመጣ ተስፋ መቁረጥ እና የፖለቲካ ተጋላጭነት አንጻር “ሰዎች የተቀረጸላቸውን ትርክት እንዳያፈርሱ ለማድረግ የተፈጸመ የማስፈራሪያ ድርጊት ነው” ሲሉ ዶ/ር ሲመንስ አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X