ናይጄሪያ እና ቤኒን የድንበር ደህንነትና ንግድን ለማሳደግ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ አጋርነታቸውን አጠናከሩ

ሰብስክራይብ

ናይጄሪያ እና ቤኒን የድንበር ደህንነትና ንግድን ለማሳደግ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ አጋርነታቸውን አጠናከሩ

የናይጄሪያ ጉምሩክ አገልግሎት እና የቤኒን አቻው የጋራ ድንበር ጥበቃን ለማጠናከር፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመግታት እና ሕጋዊ ንግድን ለማሳለጥ በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ ዙሪያ አጋርነት ፈጥረዋል።

"የሴሜ ድንበር ወሳኝ የንግድ ኮሪደር ሆኖ የቆየና በርካታ ተግዳሮቶችን ያስተናገደ ነው። በዚህ የጂኦስፓሻል ጥረት አንዳንድ ችግሮችን በመፍታት ገቢያችንን ማሳደግ እንችላለን" ሲሉ የሴሜ አካባቢ የጉምሩክ ተቆጣጣሪ አብዱላሂ ካይላ ገልጸዋል።

ተነሳሽነቱ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየትና ለሚካሄዱ ሥራዎች መኮንኖችን በስልታዊ መንገድ ለማሰማራት እንዲሁም የዓለም ጉምሩክ ድርጅትን የሳተላይት መረጃዎች በመጠቀም የናይጄሪያ የጉምሩክ የድንበር አስተዳደር መተግበሪያን ለመሞከር ያለመ መሆኑን የናይጄሪያ የጉሙሩክ አገልግሎት የጂኦስፓሻል ምክትል ኃላፊ ላባራን አህመድ ገልጸዋል።

“በቅርቡ ከፍተኛ የሥልጠና ፕሮግራም ያካሄድን ሲሆን ግብፅ፣ ሴኔጋል፣ ኬንያ እና ማሊን ጨምሮ ሌሎች 19 የአፍሪካ ሀገራት የጉምሩክ አስተዳደሮች የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመዋጋት ይህንን የቴክኖሎጂ መሣሪያ ለመጠቀም ወስነዋል” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0