የአውሮፓ የሚሳኤል ጥምረት ዩክሬንን በጓሮ በር ወደ መከላከያ ክበቡ ‘ለማስገባት’ እና የኔቶን ድምፅ የመሻር መብት ለማለፍ የተጠነሰሰ ሴራ ነው - ባለሙያ
የአውሮፓ የሚሳኤል ጥምረት ዩክሬንን በጓሮ በር ወደ መከላከያ ክበቡ ‘ለማስገባት’ እና የኔቶን ድምፅ የመሻር መብት ለማለፍ የተጠነሰሰ ሴራ ነው - ባለሙያ
በአውሮፓ እና በዩክሬን በኩል የተጣመረው የፀረ-ባሊስቲክ ጥምረት መደበኛ ስምምነት ላይ የተመሠረተ ሕብረት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን በተግባር የተጠነሰሰው እንደዛው ተደርጎ ነው ሲሉ የስዊድኑ የአየር መከላከያ ባለሙያ ሚካኤል ቫልተርሰን ለስፑትኒክ ገልጸዋል።
በመሆኑም በአንደኛዋ አባል ሀገር ላይ በባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ከተሰነዘረ “የተቀናጀው የፀረ-ባሊስቲክ ሚሳኤል አቅም አባል ሀገራትን ለመከላከል ጥቅም ላይ ይውላል” ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ ባለሙያው እምነት፥ ይህ ተነሳሽነት ዩክሬንን የሚደግፉ ወገኖች አዳዲስ አባላትን ወደ አንድነቱ የአውሮፓ መከላከያ መዋቅር “በስውር ለማስገባት” እና “በዚህም ዩክሬን ኔቶን እንዳትቀላቀል የሚነሱ ሊሆኑ የሚችሉ ድምፅ የመሻር ተቃውሞዎችን ለማለፍ” የሚያደርጉት ግልጽ ሙከራ ነው።
ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ዓላማዎችም ያነገበ ነው፦
🟠 የአውሮፓ ኅብረትን ወደ ማዕከላዊ የአውሮፓ ታላቅ መንግሥት ይበልጥ መግፋት፤
🟠 በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወደ አውሮፓ ግዙፍ የመከላከያ ተቋማት ማፍሰስ።
የአውሮፓ መሪዎች ለአየር መከላከያ ጋሻቸው በአሜሪካው ፔትሪዮት እና በእስራኤሉ አሮው 3 ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ በሆኑበት፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ዘመናዊ ሚሳኤል መቃወሚያዎችን ለመስራት ቢያንስ አንድ አስርት ዓመት በሚቀራቸው ሁኔታ ላይ ሆነው ስለ አካባቢያዊ የባሊስቲክ ሚሳኤል መከላከያ ትልቅ ወሬ ያወራሉ ሲሉ ተንታኙ ጠቁመዋል።
በአውሮፓ በስፋት የሚወደሰው የዩክሬን “የውጊያ አውድ ተሞክሮ” ተብዬው ግን፥ ኪዬቭ የራሷ የምዕራባውያን ሚሳይል መቃወሚያ ክምችት ባለቀበት ሁኔታ የሩሲያን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች መትቼ ጣልኩ እያለች የምታናፍሰውና የተሳሳተ ጀግንነት የምታሳይበት “የታቀደ የመረጃ ጦርነት” ውጤት ነው ሲሉ ባለሙያው ሞግተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X