ሕንድ ኢትዮጵያን ተምሳሌት በማድረግ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዕቅድ ተግባራዊ ልታደርግ ነው
19:49 14.07.2026 (የተሻሻለ: 19:54 14.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሕንድ ኢትዮጵያን ተምሳሌት በማድረግ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዕቅድ ተግባራዊ ልታደርግ ነው
ሕንድ የአየር ብክለትን ለመዋጋት የኒው ዴልሂን ከተማ ተሽከርካሪዎች ደረጃ በደረጃ ወደ ኤሌክትሪክ ብቻ ለመቀየር የጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠች ሲሆን፤ ለዚህም የኢትዮጵያን እርምጃ እንደ አርአያነት ጠቅሳለች።
በዚህም መሰረት ከመጪው የጎርጎሮሳውያኑ ጥር 1 ቀን 2027 ጀምሮ በዴልሂ የሚመዘገቡ አዳዲስ ባለሦስት እግር (ባጃጅ) እና ቀላል የንግድ ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ብቻ ይሆናሉ ተብሏል። በተጨማሪም እ.አ.አ. ሚያዝያ 1 ቀን 2028 ጀምሮ አዳዲስ የነዳጅ ባለሁለት እግር (ሞተርሳይክል) ምዝገባ ሙሉ በሙሉ እንደሚቆም ተመላክቷል።
እስከ መጋቢት 31፣ 2030 ድረስም በከተማዋ ያሉ አጠቃላይ ተሽከርካሪዎችን 30 በመቶ ወደ ኤሌክትሪክ ለማድረስ ግብ መቀመጡን የሕንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ሆኖም የዴልሂ የኤሌክትሪክ ኃይል ከከሰል እና ከጋዝ የሚመነጭ መሆኑ፣ በነዳጅ ሞተሮችና ባጃጆች የሚተዳደሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ገቢ ላይ ጫና መፍጠሩ በተግዳሮትነት ተጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በጥር 2024 የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብ የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ማገዷ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X