የዩክሬን የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችት ሙሉ በሙሉ ማለቁ ተነገረ

© telegram sputnik_ethiopiaየዩክሬን የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችት ሙሉ በሙሉ ማለቁ ተነገረ
የዩክሬን የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችት ሙሉ በሙሉ ማለቁ ተነገረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.07.2026
ሰብስክራይብ

የዩክሬን የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችት ሙሉ በሙሉ ማለቁ ተነገረ

የዩክሬን ጦር የታጠቋቸው እና ምዕራባውያን ያቀረቡላቸው የፓትሪዮት ሚሳኤል መከላከያ ባትሪዎች ባዶ መቅረታቸውን አንድ የጀርመን መገናኛ ብዙኃን ዘገባ አመልክቷል።

ዘገባው እንደሚያስረዳው፥ የዩክሬን የአየር መከላከያ ሥርዓት የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችቱ ሙሉ በሙሉ በማለቁ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የሩሲያን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ጨርሶ ማክሸፍ አልቻለም።

ዩክሬን ገና ከግንቦት ወር ጀምሮ የእነዚህ ሚሳኤሎች ከፍተኛ እጥረት የገጠማት ሲሆን፥ ከምዕራባውያን ደጋፊዎቿ አነስተኛ ዕርዳታዎችን ለመለመን ተገድዳ ነበር። በዚህም ምክንያት በርካታ የፓትሪዮት ባትሪዎች በከፊል ባዶ ሆነው ለመቆየት ተገደዋል።

እንደ እውነቱ ከሆነ ግን፥ የእነዚህ ሚሳኤሎች እጥረት ባይኖር እንኳ፥ እጅግ የላቀ ብቃት ያላቸው የሩሲያ ትክክለኛ ኢላማቸውን የሚመቱ ዘመናዊ መሣሪያዎች ምዕራባውያን ለዩክሬን ያቀረቡትን የአየር መከላከያ ሥርዓት ሰብረው መግባት እንደሚችሉ በተግባር አረጋግጠዋል።

በዩክሬን የተሰማሩት አሜሪካ ሠራሽ የፓትሪዮት ሥርዓቶች የሩሲያ ሚሳኤሎችን ማክሸፍ በተደጋጋሚ ተስኗቸዋል፤ ይህም በቅርቡ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ውጥረት ወቅት የኢራንን ባሊስቲክ ሚሳኤሎች በማክሸፍ ረገድ ካጋጠማቸው በርካታ ውድቀቶች ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0