"የማርበርግና የኤምፖክስ ምርመራዎችን በራሳችን አቅም፣ ባለሙያዎችና በሀገራችን መመርመር ችለናል" - የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
17:05 14.07.2026 (የተሻሻለ: 17:14 14.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"የማርበርግና የኤምፖክስ ምርመራዎችን በራሳችን አቅም፣ ባለሙያዎችና በሀገራችን መመርመር ችለናል" - የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ኢንስቲትዩቱ የተመሠረተበትን 100ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል የአከባበር ሥነ-ስርዓት በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫን የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ኢንስቲትዩቱ ከአኅጉሪቱ ቀዳሚ እና ከአፍሪካ ሲዲሲ ዕውቅና ካገኙ የልህቀት ማዕከላት መካከል አንዱ ነው ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ በበኩላቸው፣ ኮቪድ ወቅት ናሙናዎች ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች የውጭ ሀገራት ይላኩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
“አሁን ግን ከኮቪድ የተሻለ የላብራቶሪ አቅም የሚጠይቁትን የማርበርግና የኤምፖክስ ምርመራዎችን በራሳችን አቅም፣ በራሳችን ባለሙያዎች፣ በሀገራችን መመርመር ችለናል” ሲሉ ከላብራቶሪ ነፃነት አልፎ ከሀገራዊ ሉዓላዊነት ጋር በእጅጉ እንደሚቆራኝ ጠቅሰዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ፣ ሩሲያ በኢትዮጵያ የላብራቶሪ አገልግሎት አጀማመር የጎላ ድርሻ እንደነበራት ጠቁመዋል።
ከሐሙስ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በሚከበረው የኢንስቲትዩቱ የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል ከ20 በላይ ጥናትና ምርምሮች እንደሚቀርቡ እና 5ኛው የጤና ሳይንስ እንደሚካሄድ ተገለጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X