የኢትዮጵያ የግብርና ልዑክ የቻይናን ዘመናዊ የግብርና አሰራሮች ልምድ ለመቅሰም እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት አደረገ
15:55 14.07.2026 (የተሻሻለ: 16:34 14.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የግብርና ልዑክ የቻይናን ዘመናዊ የግብርና አሰራሮች ልምድ ለመቅሰም እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት አደረገ
ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከተጠሪ ተቋማትና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ የግብርና ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በቻይና የልምድ ልውውጥ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቅሰም ጉብኝት ማድረጋቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጉብኝቱ የተመለከቱት ዋና ዋና ዘርፎች፦
በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የእንጉዳይ፣ የዶሮ፣ የወተት እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፤
የግብርና ሜካናይዜሽን አጠቃቀም እና የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር የሚያደርገው ልዩ ጥምረት፤
በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች።
ጉብኝቱ የድህነት ቅነሳን እና የገጠር ልማትን ለማፋጠን የሚያግዙ አዳዲስ አሰራሮችን በመለየት በኤክስቴንሽን፣ በምርምር፣ በኢንቨስትመንት እና በተሻሻለ የገበያ ተደራሽነት ላይ የኢትዮጵያና ቻይናን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia