ሩሲያ ከቻድ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች ሙሉ በሙሉ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ

ሩሲያ ከቻድ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች ሙሉ በሙሉ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ
ሰርጌ ላቭሮቭ በሞስኮ ከቻድ አቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የተሰጡ ሌሎች ዋና ዋና መግለጫዎች፦
በሳኅል ቀጣና የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች፣ በሩሲያ እና በሳኅል መካከል ያለውን ትብብር ለማደናቀፍ በሚጥሩ የቀድሞ ቅኝ ገዥ ኃይላት ይደገፋሉ፡፡
ሩሲያ እና ቻድ በአፍሪካ ግጭቶች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፤ ይህም የአህጉሪቱን የደኅንነት ችግሮች አፍሪካውያን ራሳቸው መፍታት አለባቸው የሚል ነው፡፡
የሩሲያ እና ቻድ ግንኙነት አሁን ላለበት ደረጃ የበቃው በ2024 የፕሬዚዳንት ዴቢ በሞስኮ እንዲሁም የላቭሮቭ በንጃሜና ባደረጓቸው ጉብኝቶች ወቅት ነው፡፡
በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የፀረ-ሽብርተኝነት ትብብር አስፈላጊነት በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ዳግም ይረጋገጣል፡፡
የቻድ ፕሬዚዳንት በሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በአካል ይሳተፋሉ፡፡
ሩሲያ ምንም ዓይነት ሁኔታ ቢፈጠር ለአፍሪካ ሀገራት የምግብ አቅርቦት ግዴታዎቿን ትወጣለች፡፡
አውሮፓ እና ዩክሬን አሜሪካ በአላስካ ከተደረሰው የሩሲያ-አሜሪካ ስምምነት ራሷን እንድታገል ለማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አድርገዋል፡፡
ሩሲያ እና ቻድ የዲፕሎማቲክ እና የአገልግሎት ፓስፖርት ላላቸው ዜጎች ያለቪዛ መጓዝ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X