የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሊው ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
09:56 14.07.2026 (የተሻሻለ: 10:14 14.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሊው ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ በመገኘት ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጄኔራል አሲሚ ጎይታ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ኅብረቱ አስታውቋል።
ኅብረቱ ማሊን በሰብአዊና ልማት መስኮች ለመደገፍ፣ መረጋጋትን ለማስፈን እና ወደ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመለስ ለምታደርገው ጥረት ከጎኗ እንደሚቆም ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል።
አክለውም ማሊ ሽብርተኝነትን ለመዋጋትና መረጋጋትን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሊቀመንበሩ፤ ድንበር የለሽ የሆነውን የሽብር ሥጋት ለመመከት የጋራና ተከታታይነት ያለው ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሬዚዳንት ጎይታ በበኩላቸው ጉብኝቱ የኅብረቱን ጠንካራ ደጋፊነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ማሊ ከኅብረቱ ጋር በጋራ ጥቅሞች ላይ በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ከመገናኘታቸው አስቀድሞ ከማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ ጋር መወያየታቸው ታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia