የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.07.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

 

በመጪው ጥቅምት ወር በሞስኮ የሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በአኅጉሪቱ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋግጥ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ባለሙያው ጥላሁን ሊበን ገለጹ።

 

አፍሪካ “ወርቅ መሬት” ያላት ብትሆንም በመሪዎች ክፍተትና በውጭ ጫና ምክንያት ተጠቃሚ መሆን አለመቻሏን የገለጹት ባለሙያው፣ ይህ ጉባኤ ግንኙነቱን በማሳደግ ረገድ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።

 

“በምዕራባውያን ተጽዕኖ ምክንያት አፍሪካ የራሷን ሀብት መጠቀም አልቻለችም። ከዚህ አንጻር ደግሞ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደ አኅጉር በማጠናከር፣ በተለይም ከወታደራዊና ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አንጻር የራሱን ሚና ስለሚጫወት በተናጠል የራሱ የሆነ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።”

 

ሩሲያ አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እየሠራች ያለች ሀገር እንደመሆኗ የመጪው ጉባኤ ትኩረት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

 

“ሩሲያ አሁን ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደምም አፍሪካ ቋሚ ወንበር እንዲኖራት እየሠራች ያለች ሀገር ነች።” ያሉ ሲሆን በተለይም በመጪው ጥቅምት ላይ የሚደረገው ጉባኤ ይህንን መነሻ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0