- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት፦ የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት

ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት፦ የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት
ሰብስክራይብ
“ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስረዓት መፈጠር በተለይም ለአፍሪካ አማራጭ የሌው ጉዳይ ነው [...] ሩሲያም ይህንን ነገር ይዛ መቅረቧ አስፈላጊ ነው [...] ሰርጌ ላቭሮቭ ያንሱት እና ስለአፍሪካ ሁለንተናዊ ነፃነት የሚያወሳው ‘የአፍሪካ ዳግም መነቃቃት’ አፍሪካውያን የምንቀበለው ሲሆን፣ ሩሲያ ፍትሃዊ የዓለም ስረዓት እንዲፈጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ በቀዳሚነት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2026 በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያደረጉትን ከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶ መነሻ አድርገን የይፋዊ የሥራ ጉብኝቶቹን ስትራቴጂካዊ አንድምታዎች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሐሳባቸዉን የሚያጋሩን በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር መምህር፣ ተማራማሪ ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ናቸው። በተከታዩ ጉዳያችን ደግሞ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2026 የጀመረዉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ ከብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ጋር የተደረገን አጠር ያለ ቆይታ ይዞላችሁ ይቀርባል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0