ኤርትራዊው ብስክሌተኛ በ«ወርቃማ አበቦች ባሕር» በተካሄደው የቻይና ፕሮፌሽናል የሳይክል ውድድር ላይ 3ኛውን ምዕራፍ አሸነፈ

ሰብስክራይብ

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ በ«ወርቃማ አበቦች ባሕር» በተካሄደው የቻይና ፕሮፌሽናል የሳይክል ውድድር ላይ 3ኛውን ምዕራፍ አሸነፈ

ሄኖክ ሙሉብርሃን 25ኛው የ«ቱር ኦፍ ማግኒፊሰንት ቺንግሃይ» ውድድር ሦስተኛ ምዕራፍ ላይ አስደናቂ በሆነ የፍጥነት ፉክክር አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ተፎካካሪዎቹ ከስምንቱ ምዕራፎች መካከል ለአራተኛው ምዕራፍ እየተዘጋጁ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፤ ሄኖክ በአጠቃላይ ደረጃ በመሪነት ላይ ካለው ብስክሌተኛ በ1 ሰከንድ ብቻ ዘግይቶ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።

የሦስተኛው ምዕራፍ የመጀመሪያዎቹ አምስት አሸናፊዎች፦

ሄኖክ ሙሉብርሃን (ኤርትራ)

ጆናታን ክሌቨር ካይሴዶ ሴፔዳ (ኤኳዶር)

አንቶኒዮ ኤሪክ ፋጉንዴዝ ሊማ (ኡራጓይ)

ጃን ካስቴሎን ሪባልታ (ስፔን)

አሌክስ ቶሊዮ (ኢጣሊያ)

በዘንድሮው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ብስክሌት ውድድር ላይ ከ12 ሀገራት የተውጣጡ 22 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ማራኪ በሆኑ የተፈጥሮ ዕይታዎች ውስጥ ከንፋስ ጋር እየተሻሙ ወደፊት በመገስገስ ላይ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
ኤርትራዊው ብስክሌተኛ በ«ወርቃማ አበቦች ባሕር» በተካሄደው የቻይና ፕሮፌሽናል የሳይክል ውድድር ላይ 3ኛውን ምዕራፍ አሸነፈ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
ኤርትራዊው ብስክሌተኛ በ«ወርቃማ አበቦች ባሕር» በተካሄደው የቻይና ፕሮፌሽናል የሳይክል ውድድር ላይ 3ኛውን ምዕራፍ አሸነፈ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0