ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሟቹ የቀድሞ የኳታር አሚር ለቅሶ ለመድረስ ዶሃ ደረሱ - ዘገባ

© telegram sputnik_ethiopiaጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሟቹ የቀድሞ የኳታር አሚር ለቅሶ ለመድረስ ዶሃ ደረሱ - ዘገባ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሟቹ የቀድሞ የኳታር አሚር ለቅሶ ለመድረስ ዶሃ ደረሱ - ዘገባ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2026
ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሟቹ የቀድሞ የኳታር አሚር ለቅሶ ለመድረስ ዶሃ ደረሱ - ዘገባ

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሃማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን ተከትሎ የተሰማቸውን ሐዘን ለመግለጽ ዛሬ ሰኞ ዶሃ መድረሳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ በኳታር ትራንስፖርት ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱላህ እና በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል ኢብራሂም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ​“የእሳቸው ማለፍ ለአፍሪካም ሆነ ለመላው ቀጣና ትልቅ ኪሳራ ነው” ነው ሲሉ የኢሚሩ ሕልፈተ ሕይወት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የሐዘን መልዕክት ገልጸዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0