የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ የኃይል ገበያ ለማስጀመር የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከዓለም ባንክ አገኘ

© telegram sputnik_ethiopiaየምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ የኃይል ገበያ ለማስጀመር የ1
የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ የኃይል ገበያ ለማስጀመር የ1 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.07.2026
ሰብስክራይብ

የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ የኃይል ገበያ ለማስጀመር የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከዓለም ባንክ አገኘ

የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር አባል ከሆኑ 13 ሀገራት የተውጣጡ የኢነርጂ ሚኒስትሮች፣ ሙሉ በሙሉ የተዋሃደ ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ገበያ ትግበራን ለማፋጠን በይፋ ተስማምተዋል።

ሚኒስትሮቹ በአኀጉሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ የሚያስችለውን ታላቅ ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ንግድ ለማመቻቸት የሚያስፈልጉትን የቁጥጥር እና የመሰረተ ልማት ማዕቀፎች አፅድቀዋል።

ሉዓላዊ መንግሥታት የኤሌክትሪክ ኃይልን በነፃነትና በፍትሐዊነት መግዛትና መሸጥ ለማስቻል የቀረጥ ሥርዓትን አንድ ወጥ ማድረግ፣ የሕግ ማዕቀፎችን ማስማማት እና አስተማማኝ የንግድ መድረኮችን መፍጠር ወሳኝ እርምጃዎች እንደሆኑ በባለሙያዎች ተመለካቷል ሲል የውጭ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0