በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ዓመታት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ ተነሳ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ዓመታት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ ተነሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባደረገው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገውን የብድር ዕድገት ጣሪያ ማንሳቱንና ገበያ መር የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓቱን እንደሚያጠናክር አስታውቋል፡፡

ሆኖም የብድር ገደቡ መነሳትን ተከትሎ ባንኮች ከልክ በላይ በማበደር ግሽበት እንዳይቀሰቅሱ፣ ብሔራዊ ባንክ እንደየተቋማቱ የብድርና ቁጠባ ጥምርታ መሠረት የተለየ የማስቀመጫ ፈንድ ግዴታ ሊጥል እንደሚችል የባንኩ ገዢ እዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ባንኩ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ግዜ የገንዘብ ዝውውርን ለማጥበቅ እና ግሽበትን ለመቆጣጠር መደበኛ የባንክ ወለድ ምጣኔን ከ15% ወደ 16% ከፍ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

ሌሎች ውሳኔዎች፦

ላኪዎች ያገኙትን የውጭ ምንዛሬ ለባንክ ገቢ የማድረግ ግዴታ ከ 50% ወደ 30% ዝቅ እንዲል በማድረግ 70% ማቆየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ግብይት የሚያስከፍሉት የኮሚሽን ምጣኔ ከ 2.5% ወደ 1.5% ቀንሷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታህሳስ ወር ወደ ነጠላ አኃዝ ዝቅ ብሎ የነበረው የሀገሪቱ ጠቅላላ የዋጋ ግሽበት፣ በአሜሪካ እና ኢራን ግጭት ሳቢያ በተፈጠረው የዓለም አቀፍ ነዳጅና ትራንስፖርት ዋጋ ንረት ምክንያት በግንቦት ወር ወደ 13.4% ማሻቀቡ ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0