ሳዑዲ ዓረቢያ በየመን ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የአየር ጥቃት ፈፅማለች ሲል የሁቲ ሚዲያ ገለጸ

ሰብስክራይብ

ሳዑዲ ዓረቢያ በየመን ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የአየር ጥቃት ፈፅማለች ሲል የሁቲ ሚዲያ ገለጸ

ከሁቲ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መገናኛ ብዙኃን በሰንዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸውን የዘገቡ ሲሆን፤ ‘አል ማያዲን’ የተባለው የዜና ወኪል ጥቃቱ በሳውዲ አውሮፕላኖች የተፈጸመ መሆኑን አመላክቷል።

የየመን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፥ የአውሮፕላን ማረፊያው ማኮብኮቢያ ኢላማ የተደረገው የኢራን አውሮፕላን እንዳያርፍ ለመከላከል እንደሆነና ይህም አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ወደ ሆዴዳ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቀይር አስገድዶታል ብሏል።

አንሳር አላህ (ሁቲዎች) ሳውዲ አረቢያን አዲስ ጦርነት በመክፈት የከሰሱ ሲሆን፥ የውጥረት ማርገቢያው ጊዜ ማክተሙን በይፋ አውጀዋል። ጥቃቶቹ “ያለ ምላሽ አይቀሩም” ሲሉ ያስጠነቀቁት ሁቲዎቹ፤ ሪያድ ለሚመጣው ማናቸውም መዘዝ ሙሉ ኃላፊነቱን ትወስዳለች ብለዋል።

ሳውዲ አረቢያ እስካሁን ድረስ ስለቀረቡት ሪፖርቶች በይፋ የሰጠችው ምላሽ የለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0